1009 S Uvalda St Aurora, CO 80012
Close
PO Box 471594, Aurora, CO 80047

የእምነት መግለጫ

• መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በእግዚአብሔር ምሪት በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት
መጽሐፍ መሆኑን እናምናለን። 2 ኛ ጢሞቴዎስ 3:16-17 ፤ 1 ኛ ጴጥሮስ 1:23-25 ፤
ዕብራውያን 4:12
• በስላሴ ወይም በእግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላከነት
እናምናለን። ማቴዎስ 28:19 ፤ ዮሐንስ 1:1 እና 14
• በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን።
o የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሉቃስ 1:35 ፤ ዮሐንስ 1:18 ፤ ዮሐንስ 20:27-
29 ፤ ሮሜ 2:5-8 ፤ ቆላስይስ 1:15-16
o ከድንግል መወለዱን ማቴዎስ 9:27-33 ፤ ማቴዎስ 28:18-20 ፤ ሥራ
10:34-38
o ያለ ኃጢአት መኖሩን 1 ኛ ጴጥሮስ 2:22 ፤ 2 ኛ ቆሮንቶስ 5:21 ፤ ዕብራውያ
4:15 ፤ 1 ኛ ዮሐንስ 3:5 ፤ ማቴዎስ 27:24
o በቃል እና በስራ የእግዚአብሔርን ኃይል እና ስልጣን በምድር ላይ ማሳየቱን
ማቴዎስ 9:27-33 ፤ ሥራ 10:34-38 ፤ ማቴዎስ 28:18-20
o በመስቀል ላይ ስለ እኛ መሞቱን ሉቃስ 23:44-46 ፤ 1 ኛ ጴጥሮስ 2:24
o በሶስተኛውም ቀን ከሙታን መነሳቱን 1 ኛ ቆሮንቶስ 5:14 ፤ ማቴዎስ
16:21 ፤ ዮሐንስ 2:20 ሥራ 2:24 እና 31 የሰው ልጆችን ድነት ፈጽሞ በአብ
ቀኝ መቀመጡን ሮሜ 8:34 ፤ ቆላስይስ 3:1 ፤ ኤፌሶን 1:20 ፤ ዕብራውያን
1:3
o አማኞችን ወይም ቤተክርስቲያንን ለመውሰድ ዳግም
እንደሚመጣ ( ንጥቀት ) 1 ኛ ቆሮንቶስ 15:51-52 ፤ 1 ኛ ተሰሎንቄ 4:16-
17 ፤ 2 ኛ ተሰሎንቄ 2:1 ፤ ዮሐንስ 14:3-4 ፤ ዕብራውያን 9:28
• መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል የሆነና በዚህ
ዘመን ደግሞም ለዘላለም ከቅዱሳን ጋርና በቅዱሳን ውስጥ የሚኖረው ነው።
ዮሐንስ 14 ፡ 17 መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው።
• መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ነው። ኢዮብ 33 ፡ 4 መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ ማንነት
ያለው ነው። ኤፌሶን 4 ፡ 30
• ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል እንደተፈጠረ ነገር ግን እግዚአብሔርን
ባለመታዘዝ ኃጢአት መስራቱ እና የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ የመዳኛ መንገድ መሆኑን እናምናለን። ዘፍጥረት 1:26-31 ፤ ዘፍጥረት 3:1-7 ፤
ሮሜ 5:12-21
• የሰው ልጆች ኃጢአት ድነት የሚፈጸመው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ
መሆኑን፤ ይህን ድነት ሰዎች የሚቀበሉት በራሳቸው ስራ ሳይሆን ኢየሱስ ጌታ
እንደሆነ በአፋቸው ሲመሰክሩና እግዚአብሔርም
• ከሙታን እንዳስነሳው በልባቸው ሲያምኑ እንደሆነ እናምናለን፡፤ ሮሜ . 10:9 ፤
ሮሜ 8:11
• የውሃ ጥምቀት አማኞች ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሞታቸውን፤ ከእርሱ ጋር
ለአዲስ ህይወት መነሳታቸውን የሚመሰክሩበት መንፈሳዊ ስርዓት እንደሆነ
እናምናለን። ማቴዎስ 28:19 ፤ ሥራ 10:47-48 ፤ ሮሜ 6:4
• የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ እና አማኞች ህይወታቸው ኃይል
የተሞላ እንዲሆን ስለ ጌታ ለመመስከርም ድፍረትና አቅም እንደሚሰጣቸው
እናምናለን። ሉቃስ 24:49 ፤ ሥራ 1:8 ፤ 2:38-39 ፤ 10:44-46 ፤ 11:14-16 ፤ 15:7-
9 ፤ 1 ኛ ቆሮንቶስ 12:1-31
• ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል እንደሆነች እና ኢየሱስ የጀመረውን ስራ በምድር
ላይ የምትፈጽም ደግሞም በውስጧ ያሉ አማኞች በአካሉ ውስጥ እንደብልት
የተለያየ ድርሻ እንዳላቸው እናምናለን። ኤፌሶን 1:22 ፤ ኤፌሶን 2:19-22 ፤ ሮሜ
12:3-8
• ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝ አድርገው የተቀበሉ ለዘላለም ከጌታ ጋር እንደሚኖሩ
ስጦታውን ያልተቀበሉ ግን በእሳት ባህር እንደሚጣሉ እናምናለን። ራእይ 19:20 ፤
ራእይ 20:10-15
• ኢየሱስ በንጥቀት ከሄዱ ቅዱሳን ጋር እንደሚገለጥ ሰይጣንንና ሰራዊቱን
እንደሚያሸንፍ በምድር ላይም አንድ ሺህ ዓመት እንደሚገዛ ከዚያም በኋላ አዲስ
ሰማይና ምድር እንደሚሆን እናምናለን። 2 ጢሞቴዎስ 1:7 ፤ ራእይ 19:11-16 ፤
20:1-7 ፤ እና ራእይ 21
• ጋብቻ በሁለት ተቃራኒ ጾታ ባላቸው ሰዎች ማለትም በወንድና በሴት መካከል ብቻ
እንደሚፈጸም፤ ቤተሰብና ማህበረሰብ የሚወለደው በዚህ ጋብቻ ውስጥ እንደሆነ
እናምናለን። ዘፍጥረት 2:24 ፤ 1 ቆሮንቶስ 6:9-11 ፤ 1 ጢሞቴዎስ . 1:9-11

 

Want To Be New Member? Just Join Us

We have a strong sense of community with parishioners.